ሂውማን ራይትስ ዎች የሲቪል ማኅበራት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እንዲሻር ጥሪ አቀረበ
ሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ የሕግ አውጪዎች ለመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ሰፊ የሥራ ገደብ የሚጥለውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ውድቅ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ። ድርጅቱ ይህ ረቂቅ ሕግ ከጸደቀ የሲቪል ማኅበራት ሥራን በእጅጉ እንደሚገድብ አስጠንቅቋል።
የሲቪል ማኅበራት ሕግ ረቂቅ ማሻሻያ ገና ለፓርላማ አልቀረበም ተብሏል። ሂውማን ራይትስ ዎች እንዳለው ከሆነ፣ እነዚህ ማሻሻያዎች ከፀደቁ መንግሥት በሲቪል ማኅበራት ላይ ያለውን ቁጥጥር በማጠናከር፣ የገንዘብ ድጋፍን በመገደብ እና ያለፍትህ አካል ጣልቃ ገብነት ድርጅቶችን የማገድ ወይም የመበተን ሥልጣን ይኖረዋል።
ይህ ረቂቅ ሕግ በተለይ በሀገሪቱ የዲሞክራሲ ሂደት እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ስጋት እየተገለጸ ነው።ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ለኢትዮጵያ አጋሮችም ጭምር መልዕክት አስተላልፏል፤ ይህም ማሻሻያዎቹ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ደረጃዎችን ማክበር እንዳለባቸው በግልጽ እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርቧል።
Via Capital

1 year ago