Logo
YenetaTube
በቲያትረኛዉ ትራምፕ ፉከራና ዛቻ የሚሸበር የለም ! / ሞስኮ /

የሩሲያ ባለሥልጣናት የፕሬዝደንት ትራምፕን ሩሲያ በአስቸኳይ ወደ ድርድር ካልመጣች በማዕቀብ ኢኮኖሚዋን እንደሚሽመደመድ አሜሪካ ለዩክሬን ዘመናዊ መሳርያ በማስታጠቅ ሞስኮ ላይ የሚሳኤል ዝናብ እንዲወርድባት እንደምታደርግ የሰጡትን ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ የሩሲያ ባለሥልጣናት መንቀፋቸው ተነገረ።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በ50 ቀናት ዉስጥ የተኩስ አቁም ሥምምነት ካላደረገች ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያና በንግድ ተሻራኪዎቿ ሸቀጦች ላይ ተጨማሪ ግብር እንደምትጥል ትራምፕ ትናንት አስጠንቅቀዋል።

ትራምፕ ከሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩተ ጋር ሆነዉ በሰጡት መግለጫ ሩሲያ በተቆረጠላት ጊዜ ሥምምቱንት ካልተፈራረመች ከሩሲያ ሸቀጥ በሚገዙ ሐገራት ሸቀጦች ላይ ዩናይትድ ስቴትስ 100 በመቶ የግብር ጭማሪ ትጥላለች።ትራምፕ ከማስጠንቀቂያዉ በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴትስ በNATO በኩል ለዩክሬን ጦር መሳሪያ እንደምትልክ ማስታወቃቸዉን ተከትሎ ክሬምሊን ምላሽ ሰጥቷል ።

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ማክሰኞ እለት በሰጡት መግለጫ “ለአሁኑ አንድ ነገር ግልፅ ነው፡ በዋሽንግተን፣ በኩል ጦርነቱ እንዲቀጥል ይፈለጋል ።
በኔቶ አገሮች እና በቀጥታ በብራስልስ የተደረጉ ውሳኔዎች በዩክሬን በኩል እንደ የሰላም ምልክት ሳይሆን ጦርነቱን ለመቀጠል እንደ ምልክት እየታዩ ያሉ ይመስላል” ሲል ፔስኮቭ ሩሲያ ለሰላም ንግግሮች “ዝግጁ” መሆኗን በድጋሚ ተናግሯል።

ፔሽኮቭ ትራምፕ ዩክሬን ለማስታጠቅ መወሰናቸዉ ጦርነቱን ለተጨማሪ ጊዜ ከማራዘም በስተቀር «የሚፈይደዉ የለም» ብለዋል።

የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ የዩኤስ ፕሬዝዳንት ከአውሮፓ አጋሮች በተገኘ ገንዘብ ለኪየቭ የጦር መሳሪያ ማቅረብ እንደሚጀምሩ ባሳወ የትራምፕ መግለጫ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።

ሾይጉ "ይህ አካሄድ በዶናልድ ትራምፕ ለረጅም ጊዜ ሲያራምዱ ቆይቷል, በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት "ይህ የሱ ጦርነት አይደለም" በማለት ተናግረዋል ።

የታችኛው ሀውስ ስቴት ዱማ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ሊዮኒድ ስሉትስኪ እንዳሉት ትራምፕ ከክሬምሊን ጋር ቀጥታ ግጭት ውስጥ ሳይገቡ መጠንቀቅ እንዳለበት በመግለፅ "ትራምፕ በዩክሬን ውስጥ በእውነት መሻሻልን ከፈለገ ለዜለንስኪ አገዛዝ "ቡጢውን" ማሳየት አለበት እንጂ ሩሲያን በሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ ላይ ማስፈራራት የለበትም ።ብለዋል

የቀድሞዉ የሩሲያ ፕሬዝደንት ድሚትሪ ሜድቬዴቭ በበኩላቸዉ የትራምፕን ማስጠንቀቂያ «ቲያትራዊ ቀነ-ገደብ» በማለት ነቅፈዉታል።ሜድሜዴቭ በX ገፃቸዉ በእንግሊዝኛ በፃፉት መልዕክት ሩሲያ ለትራምፕ ማስጠንቀቂያ «ደንታ የላትም» ማለታቸውን የዘገበዉ ሞስኮ ታይምስ ነዉ ።

የኔታ ቱዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.