በአፋር ክልል ዳናኪል ዲፕሬሽን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ
#ethiopia | በአፋር ክልል ዳናኪል ዲፕሬሽን ውስጥ በሚገኘው ኤርታሌ እሳተ ገሞራ ዛሬ ጠዋት ግዙፍ ፍንዳታ እንደተከሰተ የአይን እማኞች እና የአካባቢው ምንጮች አስታወቁ። ፍንዳታውን ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው አመድ እና ጭስ ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ ሲወጣ ታይቷል።
የእሳተ ገሞራው ፍንዳታ በሰፊው የጭስ ደመና ተለይቶ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል ነው የተባለው።
የኤርታሌ እሳተ ገሞራ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ንቁ እሳተ ገሞራዎች አንዱ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ጊዜያት ተመሳሳይ ፍንዳታዎች ታይተውበታል። #menahriafm
11 months ago