Logo
Getu Temesgen
72 ሚሊዮን አመት ያስቆጠረ ነው የተባለለት ግዙፍ የዳይኖሰር ቅሪተ አካል ተገኘ
#ethiopia | ሳይንቲስቶች፣ ለ72 ሚሊዮን ዓመታት ያህል ተደብቆ የቆየ ግዙፍ የዳይኖሰር ቅሪተ አካላት መሰብሰቢያ ስፍራ ወይም "መቃብር" ማግኘታቸውን አስታወቁ። ይህ ያልተለመደ ግኝት በውስጡ ከ8,000 የሚበልጡ የዳይኖሰር አጥንቶችን የያዘ ሲሆን፣ ስለ ጥንት ዘመን ህይወት እና ስለ ግዙፍ ፍጥረታት አኗኗር አዲስ መረጃዎችን የሚሰጥ ታላቅ ሳይንሳዊ ክስተት ነው ተብሎለታል።

የቅሪተ አካል ተመራማሪዎቹ እንዳስታወቁት፣ ይህ ግኝት በተለያዩ የዳይኖሰር ዝርያዎች የተውጣጡ አጥንቶችን ያካተተ ነው ብለዋል።

የዚህ ዓይነቱ ሰፊና በርካታ ቅሪተ አካላት በአንድ ቦታ መገኘት፣ ሳይንቲስቶች የዳይኖሰሮችን ማህበራዊ አኗኗር፣ ሞዴላቸውን እና የሞት ምክንያቶቻቸውን በጥልቀት እንዲያጠኑ ያስችላቸዋል ነው የተባለው። ለብዙ ሚሊዮን ዓመታት በምድር ውስጥ ተደብቆ የቆየው ይህ ስፍራ፣ ስለ ዳይኖሰር ዘመን ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

ይህ አዲስ ግኝት በፓሊዮንቶሎጂ (የቅሪተ አካል ሳይንስ) ዘርፍ እጅግ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን፣ ስለ ምድር ታሪክ እና በእሷ ላይ ይኖሩ ስለነበሩ ፍጥረታት ያለንን ግንዛቤ ይበልጥ ለማስፋት እንደሚረዳ ተመላክቷል፡፡ #menahriafm

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.