Logo
YenetaTube
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፵፭ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን ባርከው አስጀመሩ።
ጉባኤው ከጥቅምት ፫ - ፯ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 45ኛውን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በይፋ በከፈቱበት ወቅት፤ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና
ምዕመናን ከራስ ወዳድነት ወጥተው ለአንድነትና ለፍቅር ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረቡ።

ቅዱስነታቸው የጉባኤውን መከፈት አስመልክተው ባደረጉት ንግግር፣ ቤተክርስቲያኒቱ በአሁኑ ወቅት በርካታ ፈተናዎች እና ችግሮች እንደገጠሟት ጠቁመው፣ ለዚህም ዋናው ምክንያት የውጭ አካል ሳይሆን ራሳቸው መሆናቸውን በአጽንዖት ገልጸዋል።

"ፍቅርና አንድነት ጎድሎናል፤ ራስ ወዳድነት በዝቷል፤ ለቤተክርስቲያን ከመቆም ይልቅ ለራሳችን ጥቅም ማደላት ታይቶብናል" ያሉት ፓትርያርኩ፣ የችግሩ መሰረት ያለው በቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ወይም ሕግ ላይ ሳይሆን ሕጉን በሚያስፈጽሙት አካላት ላይ መሆኑን አመላክተዋል።

አክለውም "እርስ በርሳችን ከመዋደድ ይልቅ መነቃቀፍን መርጠናል። ስለዚህ ሁላችንም ወደ ራሳችን ተመልሰን፣ ንስሐ ገብተንና ይቅር
ተባብለን ቤተክርስቲያናችንን በአንድነት ልንጠብቅ ይገባል" በማለት አሳስበዋል። የአሁኑ ጉባኤም ዋነኛ ዓላማ እነዚህን ችግሮች
በመፍታት፣ ፍቅርን በማስፈን እና ተግቶ ለመስራት ቁርጠኝነት የሚታደስበት ሊሆን እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ከሩቅም ሆነ ከቅርብ ለመጡት የጉባኤው ተሳታፊዎች እና የቤተክርስቲያን ልጆች ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ
በመስጠት፤ እንዲሁም ጉባኤውን ለማዘጋጀት የደከሙትን አካላት በቤተክርስቲያኒቱ ስም በማመስገን የዘንድሮው 45ኛው አጠቃላይ
የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በይፋ መከፈቱን አብስረዋል።

EOTC Broadcasting Service Agency

6 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.