Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጅቡቲ አቅራቢያ አንድ ጀልባ ተገልብጦ ቢያንስ የ109 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዓለም ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ቀደም ብሎ ገልፆ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ባሰራጨው መረጃ ደግሞ ተጨማሪ የ30 ስደተኞች አስከሬን መገኘቱን ይፋ አድርጓል። በመሆኑም በዚህ አደጋ ህይ*ወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 139 ደርሷል።

ጀልባው ከጅቡቲ ተነስቶ ወደ የመን እየተጓዘ እንደነበር በህይወት የተረፉት ገልፀው፣ የተገለበጠውም ከጅቡቲ ኦቦክ ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ላይ መሆኑን አስረድተዋል። 350 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ ከነበረው ከዚህ ጀልባ 80 ኢትዮጵያውያን በህይወት መትረፋቸውን IOM ገልፆ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ባወጣው መረጃ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች በህይ*ወት መትረፋቸውን አስታውቋል። እንደመረጃው ሐሙስ ዕለት ለአርብ አጥቢያ ሌሊት በተገለበጠው ከዚህ ጀልባ፣ አሁን ያሉበት የደረሱበት ያልታወቀ 84 ስደተኞች አሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የIOM ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ፖፕ በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹ማንም ሰው ሌላ አስተማማኝ መንገድ እንደሌለ ካላመነ በስተቀር በእንዲህ አይነት ጀልባ ውስጥ አይገባም›› ብለዋል። ጨምረውም ‹‹ሌላ ጀልባ ከመገልበጡ በፊት መንግስታትና ለጋሾች አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቀርባለሁ›› በማለት አስታውቀዋል። በተያያዘ የአፍሪካ ህብረት በዚህ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ ለሟ*ች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

18 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.