Logo
TIKVAH-SPORT
“ ጩኸት ቢኖርም እኛም በማሸነፍ የራሳችንን ጩኸት እናሰማለን ” ኢንዞ ማሬስካ

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በድሉ መደሰታቸውን ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል።

ለስካይ ስፖርት ቃላቸውን የሰጡት ኢንዞ ማሬስካ “ በጣም ደስተኛ ነኝ በጨዋታው ነገሮችን አርመን አሸንፈናል "ብለዋል።

በወቅታዊ ሁኔታ “ ከሜዳችን ውጪ ስንጫወት ጫጫታ መሰማቱ ስለማይቀር መላመድ አለብን “ ሲሉ ማሬስካ ተናግረዋል።

አክለውም “ ነገሮችን መላመዱ እንዳለ ሆኖ እኛም የራሳችን ጩኸት መፍጠር አለብን እሱን ለመፍጠር ጨዋታውን ማሸነፍ ነው “ ብለዋል።

“ የቡድኑ እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ ነበር
፤ በሶስት ነጥቡ በጣም ደስተኛ ነኝ “ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

@tikvahethsport      kidusyoftahe
21 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.