ቪድዮ፦ በፓወር ፓንክ (Power Bank) አማካኝነት የተነሳው እሳት የኢንዲጎ አውሮፕላንን በድንገት እንዲያርፍ አስገደደው።
በህንድ ሀገር፣ ከዲልሂ ወደ ቼናይ እየበረረ በነበረ የኢንዲጎ አየር መንገድ በረራ ቁጥሩ 6E 6115 ላይ ተሳፋሪ በቦርሳ ይዞት የነበረ የፓወር ባንክ ከላይ ባለው የዕቃ ማስቀመጫ (Overhead bin) ውስጥ ድንገተኛ እሳት አደጋ እንዲነሳ አድርጓል።
አውሮፕላኑ ውስጥ 180 የሚጠጉ ተሳፋሪዎች እና 7 የካቢን ሰራተኞች ነበሩ።
እሳቱ በተሳፋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ግርግር የፈጠረ ሲሆን የካቢን ሰራተኞቹ ወዲያውኑ የእሳት ማጥፊያ በመጠቀም እሳቱን ማጥፋት ችለዋል።
አብራሪዎች ባላቸው የደህንነት ፕሮቶኮል መሰረት በረራውን በማዞር ሃይደራባድ በምትሰኝ ትልቅ ከተማ በሚገኝ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም አርፈዋል።
በሂደቱ በሰው ላይ የደረሰ አንዳችም ጉዳት የለም፤ ተሳፋሪዎችም ወደ መድረሻቸው ቼናይ በሌላ አማራጭ አውሮፕላን እንዲጓዙ መደረጉ ተዘግቧል።
ፓወር ባንኮች ውስጥ የሚገኙት የLithium-ion ባትሪዎች ሲጎዱ፣ ጫና ሲያርፍባቸው፣ ከመጠን በላይ ሲሞቁ ወይም ውስጣዊ የኤሌክትሪክ ብልሽት ሲገጥማቸው (ሾርት ሲያደርግ)፣ ሲበላሹ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ከፍተኛ ሙቀት በመፍጠር እሳት ሊያስነሱ አልያም ሊፈነዱ ይችላሉ።
ከላይ በዕቃ ማስቀመጫ ውስጥ በቦርሳ ሲቀመጥ ቦርሳ ውስጥ ያሉ አልባሳትን ፣ ወረቀቶችን ወይም ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮችን በማያያዝ እሳቱ ወደ ሌሎች ቦርሳዎች ወይም ቁሶች በፍጥነት ይሰፋል።
ፓወር ባንክ ከላይ ባለየአውሮፕላን ዕቃ ማስቀመጫ (Overhead bin) ወይም በታሸገ የሻንጣ ክፍል ውስጥ ማድረግ አይፈቀድም ፤ ምክንያቱም እሳት ቢነሳ እንኳን ወዲያው ላይታወቅ ይችላል። ከዛ ይልቅ በትንሽ የእጅ ዕቃ መያዣ አልያም በእጃችን አጠገባችን ብንይዝ ድንገት እሳት ቢነሳ የካቢን ሰራተኞች በፍጥነት እንዲቆጣጠሩት ይረዳል።
የምንጠቀማቸው ፓወር ባንኮችም መሰል ድንገተኛ አደጋዎችን እንዳይፈጥሩ ጥራታቸውና ደረጃቸው የተሻለ መሆን አለበት።
Video : Sudhakar Udmula
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

2 days ago