በተደጋጋሚ ጊዜ ጨለማን ተገን በማድረግ የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ20 አመት ከ10 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ
ደሳለኝ ጭናሾ የተባለው ተከሳሽ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ጦር ኃይሎች አካባቢ በተለያየ ቀናት ነው።
ተከሳሹ ጨለማን ተገን በማድረግና በአካባቢው ላይ ጥበቃዎች አለመኖራቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአንድ ግለሰብ የሞባይል ስልክ መሸጫ ሱቅ የሻተር በር ተንጠልጣይ ቁልፍን በብረት መቁረጫ መጋዝ ቆርጦ በመግባት፣ የተለያዩ ስማርት ስልኮች፣ የሞባይል ባትሪዎች፣ በሶላር የሚሰራ ሬዲዮ፣ የሞባይል ቻርጀር፣ የጆሮ ማዳመጫ ኤርፎን፣ የእጅ ሰዓቶችና የልብስ መተኮሻ ካውያ በአጠቃላይ 1 መቶ ሺህ 450 ብር የሚገመት ንብረት ሰርቆ ለመሰወር ሲሞክር በስራ ላይ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአውጉስታ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አባላት እጅ ከፍንጂ መያዙን ፖሊስ መምሪያው አስታውቋል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኃላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ በተጨማሪም በተጠቀሰው አካባቢ ከአንድ ምግብ ቤት ውስጥ የበር ቁልፍ ገንጥሎ በመግባት 18,000 ብር የሚገመቱ 3 የወንበር ዥንጥላዎችን እንደሰረቀና ከደበቀበት ቦታም መርቶ በማሳየት ንብረቱን ማስመለስ እንደተቻለ የገለፀው የአውጉስታ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ተገቢውን ምርመራ በማጣራት በተከሳሹ ላይ አቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተበትም አስታውቋል።
የተከሳሽ ደሳለኝ ጭናሾን ጉዳይ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ 3ኛ የወንጀል ችሎት የክስ መዝገቡን ከመረመረና የሰው ማስረጃዎችን ከአሰማ በኃላ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ያስተምራል፣ ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ግለሰቡ በፈፀመው ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል በሁለት መዝገቦች በ20 አመት ከ10 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።
ህብረተሰቡ መሰል ወንጀል እንዳይፈፀምበት በንግድ ቤቶች አካባቢ አስተማማኝ ጥበቃ መቅጠርና የደህንነት ካሜራ መግጠም እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ከተፈፀመም በአፋጣኝ ለፖሊስ በማመልከት ወንጀል ፈፃሚዎች እንዲያዙና በህግ አግባብ እንዲጠየቁ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል።

1 day ago