Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ተሰማ፡፡ በዚህ ሳምንት በተከናወነው ሹም ሽር ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በሚኒስትርነት እንዲመሩ መመደባቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮ ቢዝነስ ቪው እንደገለፀው ሚኒስትሯ ከቀናት በኋላ ደግሞ ሌላ ሹመት አግኝተዋል፡፡ ይህንን ሹመት ያገኙት ትልልቅ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ከሚያስተዳድረው ‹‹ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ›› ነው፡፡

እንደዘገባው ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወይዘሪት ፍሬህይወት የአገሪቱን ግዙፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ተቋም ቦርድ እንዲመሩ ተሾመዋል፡፡ በዚህም ለአመታት የመሩትንና ትልቅ ለውጥ የፈጠሩበትን ኢትዮ ቴሌኮም በዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበርነት የመምራት እድል ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡

ላለፉት 3 አመታት የኢትዮ ቴሌኮም ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር የነበሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደነበሩ የሚታወስ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ለኢትዮ ቴሌኮም የቦርድ ሊቀመንበር የሾመ ቢሆንም የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ግን እስካሁን አልመረጠም፡፡

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.