ኦሮሚያ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱን ከ105.7 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱን አስታወቀ
#fastmereja I ኦሮሚያ ባንክ በ2025/2026 የበጀት ዓመት በሁሉም ዋና ዋና ቁልፍ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ። የባንኩ 17ኛው መደበኛ እና 6ኛው አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የተካሄደ ሲሆን፤ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አስፋ ስሜ ለጉባዔው ዓመታዊ የስራ ሪፖርት አቅርበዋል። እንደ ባንኩ መግለጫ፣ የፋይናንስ ዘርፉ በአለም አቀፍ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች እየተፈተነ ቢገኝም፣ ባንኩ ለፈተናዎቹ ሳይበገር ጠቅላላ ሀብቱን ከ105.7 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል። ይህ አፈፃፀም ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ24 በመቶ እድገት አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 88.1 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታል በ14 በመቶ በማደግ 7.8 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ካፒታል ደግሞ 14 ቢሊዮን ብር ደርሷል። እንዲሁም በሂሳብ ዓመቱ 15.24 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ከዲሲፕሊን ጋር ከተመራ የወጪ አስተዳደር ጋር ተዳምሮ ከታክስ በፊት 3.82 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ተገኝቷል። ይህ የትርፍ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም የባንኩ የተበላሸ ብድር (NPLs) ምጣኔ 2.43 በመቶ በመሆን በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የተሻለ የብድር ጥራት ካላቸው ቀዳሚ ባንኮች ተርታ አሰልፎታል። የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 5.7 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ባንኩ ከአለም አቀፍ የዲጂታል ክፍያ መሪ ከሆኑት ቪዛ (Visa) እና ፕሪሚየር ስዊች ሶሉሽንስ (PSS) ጋር በመተባበር “ኦሮ ቪዛ ክላሲክ”፣ “ጎልድ” እና “ፕላቲንየም” የተሰኙ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን ለአገልግሎት አብቅቷል። በጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይም ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የኮርፖሬት ገቨርነንስ መመሪያ መሰረት ለቀጣይ 3 ዓመታት ባንኩን የሚመሩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዷል።

2 days ago