Logo
EBC
በፈተናዎች ውስጥ የበረታችው ኢትዮጵያ
***************

ኢትዮጵያ በታሪኳ ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር ያሸበረቀች የጥንካሬ ምሳሌ ናት።

በየዘመናቱ ጠላቶቿና ተቀናቃኞቿ ወድቀቷን፣ ድክመቷንና መበታተኗን አጥብቀው በሚመኙበት በዚያው ወቅት፣ እሷ ግን በተቃራኒው ይበልጥ ክንዷን አበርትታና አጠናክራ የምትገነባ ሀገር መሆኗን በተግባር አስመስክራለች።

ይህ የጽናት ጉዞ ከጥንት ጀምሮ ዓለም ፊቱን ባዞረብንና በብቸኝነት በቆምንበት ወቅት፣ እንዲሁም በዓድዋ ዘመቻ ጊዜ በዲፕሎማሲና በሴራ ሊያጠቁን ሲሞክሩ ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ፈተናውን መክተው ታሪክ ሰርተዋል።

በቅርብ ጊዜ ደግሞ ዓለም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተዘጋግቶ ተስፋ በቆረጠበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ እጅ ሳትሰጥና ሽብርክ ሳትል በተገቢው የጤና ጥንቃቄና በህዝባዊ ትብብር በመዚቃ፣ በቲያትር መማነቃቃት ወረርሽኙን ተቋቁማ ማለፍ ችላለች።

ሀገራችን የተለያዩ ዘመቻዎች ተከፍተውባት፣ ዓለም ጀርባውን ባዞረባትና ፍርደ-ገምድልነቱን ደጋግሞ ባሳያትም ጊዜ ለአንዲት ሰከንድ እንኳ አንገቷን አልደፋችም።

በመደመር መንግስት ምስረታ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግልፅ እንዳስቀመጡትም፤ በተፈጥሮ ሀብታችንና በወንዛችን የመጠቀም መብታችንን ለማስከበር ደፋ ቀና ስንል፣ የታላቁ ህዳሴ ግድባችንን ፍጻሜ ለማደናቀፍ በረጅም ገመድ አስረው ወደኋላ ሊጎትቱን ቢሞክሩም ተንገዳገድን እንጂ አልወደቅንም፤ ከእንግዲህም ቢሆን በፍጹም አንወድቅም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተናገሩት በዚህ ጥልቅ ሃሳብ ላይ እንደሚንጸባረቀው፣ ኢትዮጵያ ከአያት ቅድመ-አያቶቿ የወረሰችውን የማይበገር የማሸነፍ መንፈስ ሰንቃ በርካታ ውጫዊና ውስጣዊ ጫናዎችን ተቋቁማ አልፋለች።

ይህ ታሪክ ደግሞ ወደፊትም ሀገራችን በማንኛውም ፈተና ውስጥ አልፋ የምትገነባ ጽኑ ሀገር መሆኗን ህያው ምስክር ሆኖ ይኖራል።

በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.