በዋግ ኽምራ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተው ከባድ ድርቅ ዜጎቻችንን ለጽኑ የምግብ እጥረትና ጥም ዳርጓል።
በኤልኒኖ ክስተት ምክንያት በሰሃላ ሰየምት ወረዳ በተከሰተው ዝናብ እጥረት አርሶ አደሮች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ ለዘርና የእንስሳት መኖ እጥረት ዳርጓል።
አርሶ አደሮች በድካም የዘሩት ማሽላ፣ ጤፍና ዳጉሳ ሳይበቅል በመድረቁ የዕለት ጉርሳቸው ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።
በወረዳው ከሚገኙ ጎጦች መካከል አብዛኛዎቹ ንጹህ መጠጥ ውሃ በማጣታቸው ሰዎች እና እንስሳት ለጽኑ ጥማት ተጋልጠዋል።
በተለይ አጥቢ እና ነፍሰ ጡር እናቶች፣ እንዲሁም ሕፃናት እና አረጋውያን በምግብ እጥረት ሳቢያ ለከፍተኛ የጤና አደጋ ተገልጠዋል።
አርሶ አደሩ የዕለት ምግብ ብቻ ሳይሆን፣ ለሚቀጥለው የእርሻ ወቅት የሚሆን ዘር እና ለእንስሳቱ የሚሆን መኖ አጥቶ እየተሰቃየ ይገኛል።
የአካባቢው ማህበረሰብ " ለጊዜያዊ የምግብ ዕርዳታ ብቻ ሳይሆን ለዘር እና ለእንስሳት መኖ አስቸኳይ ድጋፍ ይደረግልን " በማለት ጥሪ አቅርቧል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

2 days ago