Logo
YenetaTube
አትሌት መስከረም ማሞ በሊዝበን ማራቶን አሸነፈች

39ኛው የሊዝበን ማራቶን ዛሬ ተካሄዷል

በሴቶች አትሌት መስከረም ማሞ 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ አሸንፋለች።

ጠጂቱ ስዩም እና በሻንኬ ኢሙሼ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣት የኢትዮጵያን የበላይነት አረጋግጠዋል።

በወንዶች ዩጋንዳዊው ማርቲን ናይቤይ ሙሳ አሸንፏል።

ኢትዮጵያዊው አትሌት ደሳለኝ ይሌ አራተኛ ወጥቷል።

አብዲ ዓሊ ሰባተኛ እና ደምሱ ገመዳ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የሊዝበን ማራቶን ከእ.አ.አ 1986 አንስቶ እየተካሄደ የሚገኘው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ነው።

የማራቶን ውድድሩ እውቅ አትሌቶች ከሚሳተፉባቸው ውድድሮች መካከል ይጠቀሳል።

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.