የኢትዮጵያ ታዳሽ ኢነርጂ ዘርፍን የሚያጠናክረው የ«ኤ ቱ ዜድ ኢነርጂስ» እና «አልፕ ሶላር/ሊጎ» የጋራ ኩባንያ በይፋ ተመሠረተ።
የኢትዮጵያን ታዳሽ የኢነርጂስ ዘርፍ ይበልጥ ለማዘመንና አቅሙን ከፍ ለማድረግ ታላቅ መሰረት የሚጥል አዲስ የጋራ ኩባንያ (Joint Venture) የምረቃ መርሐ ግብር ተካሄዷል።
«ኤ ቱ ዜድ ኢነርጂስ » (A to Z Energies) ከተባለው አገር በቀል ድርጅት ጋር፣ ዓለም አቀፍ ዝናን ካተረፉት የቻይና የኢነርጂስ እና የባትሪ ማኔጅመንት ሲስተም (BMS) ግዙፍ ካምፓኒዎች ከሆኑት ከ«አልፕ ሶላር / ሊጎ» (AlpSolarr / Ligoo) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የተመሰረተው ይህ አዲስ ኩባንያ በይፋ ስራ መጀመሩ ተበስሯል።
ኩባንያው በ50 ሚሊዮን ዶላር የሼር ማዕቀፍ የተቋቋመ ሲሆን፣ ዘመናዊ ምርቶችን በቀጥታ ለአገር ውስጥ ገበያ እና ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ማቅረብ የኩባንያው ዕቅድ ነው። IATF16949፣ ISO26262 እና ASPICE CL2ን በርካታ ዓለም አቀፍ የደህንነት እና የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቶች ያሉት አውቶሞቲቭ-ግሬድ (Vehicle-grade) ምርቶች በኩባንያው እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
ዋና አጋር የሆነው «ሊጎ» (Ligoo) እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የባትሪ ማኔጅመንት ሲስተሞችን (BMS) በማልማት የ15 ዓመታት ልምድ ያለው ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ አውቶሞቲቭ ግዙፎች ጋር በመስራት ከፍተኛ የገበያ ድርሻ አለው። ከእነዚህም መካከል BYD፣ ጂሊ (Geely)፣ ቼሪ (Chery)፣ ኤስ.ጂ.ኤም.ደብሊዩ (SGMW) እና ቴስላ (Tesla) ይገኙበታል፡፡
በድርጅቱ ከሚቀርቡ ዋና ዋና ዘመናዊ የኢነርጂ መፍትሄዎች መካከል የቤት ውስጥ (Residential) እና የንግድ/ኢንዱስትሪ (C&I) የኢነርጂስ ማከማቻ ሲስተሞች (ESS)፣ ሃይብሪድ ኢንቨርተሮች (Hybrid Inverters) እና የሃይል ፍላጎትን በዘላቂነት ለማስተናገድ የተዘጋጁ የየኢነርጂ አስተዳደር አማራጮች ስለመሆናቸው ተነግሯል።
የኤ ቱ ዜድ ኢነርጂስ መሥራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሙጂብ አስመራ በሰጡት አስተያየት፣ "ይህ ትብብር የኩባንያችን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የኢነርጂስ ተደራሽነት ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ከሊጎ እና አልፕ ሶላር ጋር በመሆን ሀገራችንን በኢነርጂስ አስተዳደር ዘርፍ የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ ቁርጠኞች ነን" ብለዋል።
ይህ የምረቃ መርሐ ግብር የሀገራችንን የኢንቨስትመንት ከፍታ የሚያሳይ አበረታች ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል። ድርጅቱ ጎተራ ፔፒሲ 300 ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ቄራ መንገድ በሚገኘው ሾው ሩም ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች የሶሻም ሚዲያ ተፅዕኖፈጣሪዎች ተገኝተዋል።

2 days ago