የኤደን ኃይሉ "የምድረ በዳ ውሃ" መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው
#ethiopia | በኢቲቪ፣ በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን እና እንዲሁም በመንፈሳዊ አገልግሎት የምትታወቀው ኤደን ኃይሉ በህይወት ያለፈችበትን መንገድ በመጽሐፍ አስፍራ ለማስነበብ ተዘጋጅታለች።
ከልጅነቷ አንስቶ ያለፈችበትን ውጣ ውረድ መጽሐፏ ላይ ተርካዋለች።
የመፅሐፉ የእርማት፣ የማስተባበር እና የአርትኦት ተግባር የተከናወነው በተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ሲሆን ደራሲ ዝናው ደነቀ የቅድመ አርትኦት ሥራውን አከናውኗል። እዝራ እጅጉ እና ታደሰ ማሞ የፍፃሜ እርማቱን ያከናወኑ ሲሆን ታሪኩ ተፅፎ ለመጠናቀቅ 1አመት በላይ እንደወሰደ ታውቋል።
ኤደን ኃይሉ ካናዳ በኑሮ፣ በመንፈሳዊ አገልግሎት እግዚአብሔር በህይወቷ ያደረገላትን ድንቅ ተኣምር በመፅሐፉ ላይ የመሰከረች ሲሆን ታሪኩም በርካታ ፎቶግራፎችን በማስረጃነት አካቷል።
መጽሐፉን ያነበቡ ባለሙያዎችም የጀርባ ሽፋን ላይ አስተያየት ያሰፈሩ ሲሆን ሀሣብ ከሰጡት መካከል ዶክተር ማሙሻ ፋንታ፣ ወንድም ንጉሤ ቡልቻ፣ሐዋርያ ዮሐንስ ግርማ እና ሰይፉ ፋንታሁን ይገኙበታል ።
ኤደን ኃይሉ ይህን የምድረ በዳ ውሃ የተሰኘ መጽሐፍ እግዚአብሔር ረድቷት ለፍፅሜ በማብቃቷ በቀዳሚት ምሥጋናዋን ለፈጣሪ አቅርባለች። መጽሐፉ በቅርቡ በካናዳ ለምረቃ የሚበቃ ሲሆን ታላላቅ ሰዎችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

3 days ago