Logo
YeneTube
የትግራይ ክልል የሕዝብ መዝሙር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ ተገለጸ።

በክልሉ አዲስ አስተዳደራዊ መዋቅር እየተዘረጋ ነው

በትግራይ ክልል መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ክልሉን ወደ ሙሉ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ የሚደረጉ አጠቃላይ የመልሶ ግንባታና የአስተዳደር መዋቅር ዘረጋ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለጸ።

ከስፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የአካባቢ አስተዳደሮችን የማጠናከርና ክፍተቶችን የመድፈን ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በከተሞች አዳዲስ ከንቲባዎች፣ በወረዳዎች አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የዞን አመራሮች እየተሰየሙና እየተመረጡ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የብዙዎችን ትኩረት የሳበው አቢይ ዜና፣ ህውሃት ለክልሉ ላለፉት 30 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውና በይዘቱ ግጭት ቀስቃሽ እንደነበር የሚነገረው የሕዝብ መዝሙር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ መሰማቱ ነው።

እንደ መረጃው ከሆነ የመዝሙሩን ግጥም አስተካክሎና ዜማውን አሻሽሎ በአዲስ መልክ የማዘጋጀት ስራ መጀመሩ የተነገረ ሲሆን፣ ይህም ክልሉን ወደ አዲስ የሰላም፣ የእድገትና የመልካም አስተዳደር ምዕራፍ ለማሸጋገር እየተደረጉ ካሉ ዋና ዋና እርምጃዎች አንዱ እንደሆነ ተመልክቷል።

@Yenetube Fikerassefa
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.