Logo
Getu Temesgen
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የእንኳን ደስ አለዎት እና የምስጋና መልእክት አስተላለፉ
#ethiopia | የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ልባዊ ምስጋናቸውን በማቅረብ ለአዲሱ የሥራ ኃላፊነታቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልእክት፣ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ለማሳደግና ለማሻሻል ያሳዩትን ከፍተኛ ትጋት፣ ቁርጠኝነት እና በጋራ የተከናወኑ ስራዎችን በላቀ ሁኔታ አንስተዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም ዶ/ር ደረጄ በተሰጣቸው አዲስ የሥራ ኃላፊነት የተሳካ፣ ፍሬያማ እና ውጤታማ የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

16 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.