በኢትዮጵያ ከ100ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቡና ይጠጣሉ ተባለ
👉ከ6 እስከ 8 ስኒ ቡናን መጠጣትም የልብ ጤናንለመጠበቅ እንደሚረዳ ተገልጿል
በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማዕከል የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ዘካሪያስ በለጠ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናሩት ኢትዮጵያ የኮፊ አረቢካ መገኛ እንዲሁም የአፍሪካ ትልቋ ቡና ላኪ ሀገር እንደመሆኗ 90 በመቶ የሚሆኑት ዜጎቿ ቡናን ይጠጣሉ። ይህም በአሀዝ ሲገለፅ ከ100ሚሊየን በላይ ሰዎች ቡናን እንደሚጠጡ ያሳያል።
በኢትዮጵያ በቡና ዙሪያ የተሰሩት ጥናቶች አናሳ ቢሆኑም በፈረንጆቹ 2026 ሀምሌ ወር የአሜሪካ የልብ ማህበር ባወጣው ሳይንሳዊ መግለጫ ላይ ስኳር፣ክሬመር ወይም ወተት ያልገባበት ንፁህ ጥቁር ቡናን ከ3እስከ 5 ኩባያ ወይም ከ6 እስከ 8 ስኒ የሚያህል ቡናን መጠጣት የልብ ጤናን ይጠብቃል ።
ጥናቱ እንደሚያሳየው በተገለፀው ልኬት ልክ መጠጣት የስኳር፣የስትሮክ እንዲሁም የልብ ድካምን በተወሰነ መልኩ እንደሚቀንስ አመላክቷል ። እንደ ዶ/ር ዘካሪያ ገለፃም ጥናቱ አስፈላጊ ማስጠንቀቂያዎችንም አካቷል ብለዋል፡፡ ከተቀመጠው መጠን በላይ ቡናን መጠጣት የልብ ምት መዛባት እና ፣ልብ ላይ አላስፈላጊ ጫናን ሊያስከትል እንደሚችል አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ስኳር እና ክሬመርን በቡና ላይ መጨመር የካሎሪን መጠንን ስለሚጨምር በልብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ተናግረዋል። እንዲሁም ጥናቱ ሌላ ተጨማሪ ነገሮችን ያካተተ ሲሆን ሀይል ሰጪ መጠጦች በጣም ከፍተኛ የካፊን መጠን ስላላቸው የደም ግፊትን ወይንም የልብ ምት መዛባትን ስለሚያስከትሉ መጠቀም እንደማይገባ ጠቁሟል።
አንዳንድ ሰዎች ቡና ሲጠጡ ትንፋሽ ማጠር ፣የልብ መጨነቅ ፣የልብ ምት መጨመር ያሳያሉ ሌሎች ደግሞ ይሄ ምልክት ላይታይባቸው ይችላል።ነገር ግን ምልክቱ የሚታይባቸው ሰዎች የቡና መጠንን መቀነስ እንዳለባቸው ጥናቱ ይጠቁማል ብለዋል ።
በተጨማሪም ህፃናት እና ነብሰጡር የሆኑ ሴቶችም በጣም አነስተኛ መጠንን እንዲጠቀሙ እና ከመጠቀማቸውም በፊት ሀኪሞቻቸውን ማማከር እንዳለባቸው ጥናቱ እንደሚገልፅ ዶ/ር ዘካሪያስ በለጠ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል Photo

12 hours ago