Logo
YeneTube
የትምባሆ ኢንዱስትሪዎችን ጣልቃ-ገብነት ለመከላከል አዲስ ረቂቅ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ

የትምባሆ ቁጥጥር ስራ በአንድ ተቋም ብቻ እንደማይሳካና የኢንዱስትሪዎችን ያልተገባ ጣልቃ-ገብነት ለመከላከል የተቀናጀ የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ ከማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ባካሄደው የ1ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ ላይ፤ ከተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና የሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ የኮሚቴ አባላት የቁጥጥር ሥራውን በተቋማቸው ዕቅድ ውስጥ አካተው እንዲመሩ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም ቁጥጥሩን ይበልጥ ለማጠናከርና ክፍተቶችን ለመሙላት በተዘጋጀው አዲስ ብሔራዊ ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተደርጎ ግብዓት ተሰብስቧል።

ፋውንዴሽኑ በበኩሉ ከትንባሆ ነፃ የሆነች ሀገር ለመፍጠር የጀመረውን ተጋድሎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጹን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@Yenetube FikerAssefa
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.