Logo
FastMereja
ቃል ኢንተርናሽናል የውበት ማሰልጠኛ ተቋም በተለያዩ በዉበት መስኮች ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች አስመረቀ!
#fastmereja :ቃል ኢንተርናሽናል የዉበት ማሰልጠኛ ተቋም ለ47ተኛ ዙር በተለያዩ የዉበት መስኮች ያሰለጠናቸዉን ከ50 በላይ ተማሪዎችን በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ።

በዛሬዉ እለት በሜካፕ፣ በጥፍር፣ በጸጉር በአይላሽ ሽፋሽፍት የውበት ሞያ ዘርፎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነዉ ያስመረቀዉ።

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የዲጂታል እና የመደበኛ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች፣ በውበት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች/የድርጅት ባለቤቶች እና የተማሪዎች ወዳጅ ዘመዶችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የቃል ኢንተርናሽናል የዉበት ማሰልጠኛ ተቋም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የውበት ትምህርት ለማድረስ ካለው ቁርጠኛነትና ትጋት ባለፈ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ እና ከፍለው መማር የማይችሉ ሴቶችን በመደገፍና በማበረታታት የሞያ ባለቤት በማድረግ ብሩህ ተስፋ ያላቸውና የፋይናንስ ነጻነት ያላቸው አምራች ዜጎች እንዲሆኑ እድሎችን በማመቻቸት ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ስመጥር ድርጅት ነው፡፡

ቃል ኢንተርናሽናል የዉበት ማሰልጠኛ ተቋም ከተለያዩ የአውሮፓ ተቋማት ጋር የሀገራችን የውበት ኢንዱስትሪ ደረጃ ለማሳደግ እና ለተማሪዎች የስራ እድሎችን ለማስፋት በስፋት እየሰራም የሚገኝ ሲሆን በአሁን ወቅት ተደራሽነቱን በማስፋት በካናዳ በተለያዩ ስቴቶች በርካታ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ትገኛለች።

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.