“ለምን ኦሮሚያ ዘፈን ታወጣለህ ተብዬ የዘረኝነት ስድብ መመልከቴ አሳዝኖኛል ” ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ
#fastmereja I ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በሥራዎቹ እና በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ሲሰነዘሩ ለነበሩ አከራካሪ አስተያየቶች ምላሽ መስጠቱን ከራሱ ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ መልእክት ለማወቅ ተችሏል። ድምፃዊው አብዛኛውን ጊዜ ከሥራዎቹ ባሻገር በቃላት ምልልሶች ውስጥ የመሳተፍ ልምድ እንደሌለው በመግለጽ፣ በቅርቡ በተመለከታቸው አንዳንድ አስተያየቶች የተሰማውን ቅሬታና ሀዘን ገልጿል።
ጃኪ ጎሲ ቀደም ሲል ባቀረባቸው በርካታ ሙዚቃዎች በአማርኛ፣ በትግርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች በመጠቀም ኢትዮጵያዊነቱን በተግባር ለማሳየት መሞከሩን አምላክቶ፣ ወደፊትም በዚህ መንገድ ከመቀጠል ወደኋላ እንደማይል አረጋግጧል። ሆኖም አሁን በለቀቀው ነጠላ ዜማ ምክንያት በተወሰኑ ወገኖች ዘንድ የሚሰነዘሩትና ዘረኝነትን የሚያስፋፉ አስተያየቶች ለትውልድ አርአያ የማይሆኑና ደስ የማያሰኙ መሆናቸውን ጠቁሟል።
“ነገሮችን ለምን በመልካም መንገድ አናይም?” ሲል ጥያቄ ያቀረበው ድምፃዊው፣ “በትንሹ ነገር እንዲህ እየተለያየን እንዴት ነው በአንድ ሀገር አንድ ሆነን መኖር የምንፈልገው?” በማለት የህብረት እና የፍቅር አስፈላጊነትን አሳስቧል። በመጨረሻም የፍቅር እና የአንድነት መልእክቱን በማስተላለፍ አድናቂዎቹ እና ህዝቡ ለተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች አዎንታዊ እይታ እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርቧል።

2 days ago