የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ የለቀቀው ተቋም 400 ሺህ ብር ተቀጣ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣንና የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በጋራ ባካሄዱት ቁጥጥር የቻይናው ካም ወይም ጂያንግዙ የተባለ ተቋም የሽንት ቤት ፈሳሽ በቀጥታ ወደ ወንዝ ሲለቅ በመገኘቱ የ400 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መቀጣቱ ተገልጿል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እንደገለጸው ድርጊቱ የአካባቢን እና የወንዞችን ንጽህና የሚበክል በመሆኑ በወጣው የደንብ መተላለፍ ደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት ተቋሙ ቅጣቱ የተጣለበት ሲሆን ወደ ወንዝ የሚለቀቀውን ፈሳሽም እንዲያስቆም ተደርጓል።
ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግሥት ተቋም የአካባቢን ንጽህና የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ያሳሰበው ባለስልጣኑ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ኅብረተሰቡ መሰል የአካባቢ ብክለት እና የደንብ መተላለፍን ሲመለከት በ 9995 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
#ዳጉ_ጆርናል

2 days ago