የኢትዮጵያ ፓስታ በፈጣን የፓስታ አገልግሎት ከአፍሪካ በአንደኝነት ደረጃ ላይ ይገኛል ተባለ
የኢትዮጵያ ፖስታ ባለፉት 132 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ104 በላይ በሀገር ውስጥ ደግሞ ከ1 ሺህ 800 በላይ መዳረሻዎች እንዳሉት አስታውቋል።
ባለፉት ሶስት ዓመታት በተተገበረው ስትራቴጂ ተቋሙ በEMS ወይም በፈጣን የፓስታ አገልግሎት ከአፍሪካ በ1ኛ፣ ከዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት የኢትዮጵያ ፖስታ የማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ማሙሽ ናቸዉ ።
56ኛው የዓለም የፖስታ ቀን እየተከበረ ባለበት ወቅት የአራዳ ፖስታ ቤት ሙዚየም ታድሶ ለህዝብ ክፍት ሆኗል ። ሙዚየሙ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም የሀገርን ታሪክና ባህል በቴምብሮች እና በጥንታዊ የፖስታ መገልገያዎች አማካኝነት ለህዝብ ለማስተወቅ ክፍት ሆኗል።የኢትዮጵያ ፖስታ የመልእክትና የእቃ ማጓጓዣ ተቋም ከመሆኑ ባለፈ ፖስታ የሀገር ባህል፣ ታሪክ፣ ተፈጥሮ፣ ሳይንስ እና የኪነ-ጥበብ አምባሳደር መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በተለይም ቴምብሮች ሀገርን፣ ባህልን፣ ታሪክን እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነትን ለትውልድ የሚያስተላልፉ ህያው ማህደሮች እንዲሁም የሀገርን ማንነት አትመው ለአለም የሚያስተዋውቁ ታላላቅ ሰነዶች ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ ሙዚየሙ ታሪካዊ የቴምብር ስብስቦች እና የተለያዩ የፖስታ ማስታወሻዎችን በተሻለ ሁኔታ ለጎብኚዎችና ለህዝብ ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል።
በተጨማሪም ሙዚየሙ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አቅራቢያ የሚገኝ እንደመሆኑ በሁሉም የሳምንቱ ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተነግሯል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል

18 hours ago