ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የሴንቸሪ ሪል እስቴት ይፋዊ የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ!
#fastmereja :- ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (ሴንቸሪ ሪል እስቴት) ተወዳጁን ድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ይፋዊ የብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ ሾመ።
ድርጅቱ አምባሳደሩን ይፋ ያደረገው "ደሞ በዚህ ላይ... ሥራዎቻችን ምስክሮቻችን!" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ልዩ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ-ግብር ላይ ነው።
በኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በብረታ ብረት እና በማዕድን ዘርፎች የ70 ዓመታት የንግድ ታሪክ ያለው ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ባለፉት 30 ዓመታት በሪል እስቴት ዘርፍ ጠንካራ ስም መገንባት ችሏል።
ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ በአዲስ አበባ 16 ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይለንግድ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ የሚሆኑ ዘመናዊ ህንፃዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል።
ከተጠናቀቁና ለባለቤቶቻቸው ከተረከቡ ፕሮጀክቶቹ መካከል በቦሌ መድኃኒያለም የሚገኘው ሴንቸሪ
ራዲያንስ፣ በቦሌ ብራስ የሚገኘው ሴንቸሪ አዲስ ትሬዠር፣ በቦሌ አትላስ የሚገኘው ሴንቸሪ ሼባ ሆምስ፣ በካሳንቺስ የሚገኘው ሴንቸሪ ሴንትራል፣ በተክለሃይማኖት የሚገኘው አስመን ተክለሃይማኖት እንዲሁም በቦሌ ቡልቡላ የሚገኘው ኦክ አፓርትመንት ይጠቀሳሉ።
ከንግድ እንቅስቃሴው በተጨማሪ ድርጅቱ ሁለገብ ማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል ለ2,000 በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣ በየካ ክፍለ ከተማ በገነባው የምግብ ማዕከል በየቀኑ ለ250 በላይ ወገኖች የምግብ አገልግሎት መስጠት፣ከ500 በላይ አረጋውያንን በቋሚነት በበጀት መደገፍ ይጠቀሳል።
እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከ50 በላይ አዳዲስ ቤቶችን ገንብቶ ማስረከብ እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ፣ በሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች (በገበታ ለትውልድ፣ በገበታ ለሀገር፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በኮሪደርልማት) ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይገኙበታል።
ሴንቸሪ ሪል እስቴት ከአዲሱ የብራንድ አምባሳደሩ ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ ጋር በመሆን በኦሎምፒያ፣ ሜክሲኮ፣ ቦሌ ሰላም መንገድ እና ሴቶች አደባባይ አካባቢ የሚያከናውናቸውን አዳዲስ ግንባታዎች አፋጥኖ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

21 hours ago