አዳዲስ ሚኒስትሮች ሊፈጸሙ የሚችሉ የሙስናና የሌብነት ድርጊቶችን የፖለቲካ ሽፋን ከመስጠት ሊቆጠቡ ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ ፡፡
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) አዲስ የተሾሙ የካቢኔ አባላት በየተቋሞቻቸው ከሥራቸው ላሉ አመራሮችና ሠራተኞች ሊፈጸሙ የሚችሉ የሙስናና የሌብነት ድርጊቶችን በትግስትና በጥበብ የመፈተሽ እንጂ፣ ጥቆማ ሲመጣ እኛ ጋር የለም በሚል የፖለቲካ ሽፋን ከመስጠት ሊቆጠቡ እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አሳሰበዋል፡፡
የምክር ቤት አባላቱ አዲሱን የካቢኔ ዛሬ ያጸደቁ ሲሆን አንድ ተሾሚ ሚኒስትር በግል ባሕሪው ስነምግባር ፣ ብቃት ያለውና ረጅም የሥራ ልምድ ቢኖራም ከሥሩ የሚመደቡ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የራሳቸውን አካሄድና አመለካከት ስለሚደብቁ ሳይታወቅ የሌብነትና አሰራር ማጭበርበር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል።
ቀደም ባሉት ዓመታት በነበሩ አሰራሮች በተወሰኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ሌብነት አለ ተብሎ በቋሚ ኮሚቴዎች ጥቆማና አስተያየት ሲሰጥ፣ የተወሰኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሚኒስቴር ዴኤታዎች ጉዳዩን ከማጣራት ይልቅ መከላከያ መልስ በማዘጋጀትና ሲከራከሩ እንደነበር አባላቱ አስታውሰዋል።
ሆኖም ግን ጉዳዩ መጨረሻ ላይ ተገልጦ ጫፍ ሲደርስ በርካታ ኃላፊዎች በሙስና ሲጠየቁና ሲታሰሩ መታየታቸውን ጠቅሰዋል።
አዳዲሶቹ ሚኒስትሮች ይኸው ልማድ በአዲሱ የካቢኔ ዘመን እንዳይደገም ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ከዙሪያቸውና ከሥራቸው ባሉ አመራሮች ላይ የሚመጡ የሌብነት ጥቆማዎችን በቀላሉ የለም ብለው ከመግፋት ይልቅ፣ በራሳቸው ማጣራትና የእርምት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የምክር ቤቱ አባላት ተሾሚዎቹ ይኸንን ተቋማዊ ጥንቃቄና የሙስና መከላከል ስልት በመከተል፣ በየመሥሪያ ቤቶቻቸው ግልጽነትና ታማኝነትን በማረጋገጥ ሀገሪቱ የምትፈልገውን ልማት፣ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
በወልደ ሐዋርያት ዘነበ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

2 days ago