Logo
Tikvah-University
#wolaitasodouniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ ለተቋሙ ፕሬዝዳንት መመደብ ይፈልጋል፡፡

ለፕሬዝዳንትነት ክፍት የሥራ መደቡ ለመወዳደር ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ 2ኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ መሰፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመስከረም 20/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ 22 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር 28 እንዲሁም አዲስ አበባ በሚገኘው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት ማመልከቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አሰፈፃሚ ስልክ ቁ.፦ 0461800602

በአዲስ አበባ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰልክ ቁ. +251912661430 / +251938362357

(ዝርዝር ማስታወቂው ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.