ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ አየር መንገድ በቴህራን አረፈ
በኢራን ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ አየር መንገድ በዋና ከተማዋ ቴህራን ማረፉን የኢራን መንግስት ብዙኃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
አሜሪካ የኢራቅ ብሔራዊ አየር መንገድ ወደ ኢራን በረራ እንዲያደርግ ልዩ የማዕቀብ ነፃ ፈቃድ መስጠቷን ተከትሎ፣ የኢራቅ አየር መንገድ አውሮፕላን ከኢራቋ ነጃፍ ከተማ ተነስቶ ቴህራን አርፏል።
የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን አውሮፕላኑ ቴህራን ሲያርፍ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ ያስተላለፈ ሲሆን በረራው ደርሶ መልስ አገልግሎት መሆኑን ገልጿል።
ባለፈው ወር የኢራቅ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አሜሪካ ለኢራቅ አየር መንገድ ወደ ኢራን በረራ እንዲያደርግ ልዩ ፈቃድ መስጠቷን አስታውቆ ነበር። የተሰጠው ፈቃድም በኢራን እና በኢራቋ ነጃፍ መካከል ለሚጓዙ መንፈሳዊ ተጓዦች የበረራ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
በሚኪያስ ጸሐዬ
#ዳጉ_ጆርናል

3 days ago