በወተት ላይ የሚታየውን የጥራት ችግር ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ ደንብ በሂደት ላይ መሆኑ ተገለጸ
👉 ረቂቅ ደንቡ ጸድቆ ወደ ስራ ሲገባ ከእርባታ እስከ ገበያ ያለውን የንግድ ሰንሰለት ጥራት ለማስጠበቅ ሚና እንደሚኖረው ተነግሯል
በወተት ምርት ፣ አያያዝና ስርጭት ላይ እየታዩ ያሉ የጥራት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ረቂቅ የህግ ማዕቀፍ ለማስጸደቅ በሂደት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በ 2018 በጀት ዓመት በተደረገ ጥናት ከወተት እርባታ ሼዶች ጀምሮ እስከ ችርቻሮ መሸጫ ሱቆች ድረስ የንፅህና ጉድለቶች መኖራቸው እንደተረጋገጠ አስታውቋል።
በእርባታ አካባቢዎች አላቢዎች ተገቢውን የደንብ ልብስ አለመልበስና የንፅህና አጠባበቅ ክፍተት መታየቱ እንዲሁም ላሞች ሲታመሙ የሚወስዱት መድኃኒት ከሰውነታቸው ሳይወጣ ወተቱ ለገበያ መቅረቡ በጥናቱ ከተለዩት አበይት ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ለወተት ማለቢያ ፣ ማጠራቀሚያ እና ማጓጓዣነት የአሉሚኒየም እቃዎችን መጠቀም ሲገባ ለጤና ጠንቅ በሆኑና ለማፅዳት አስቸጋሪ በሆኑ የፕላስቲክ ጀሪካኖች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ጸጋ ለማ ተናግረዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ ከዚህም ባሻገር በአንዳንድ አካላት ወተት ውስጥ ውሃ በመጨመር የወተቱን ተፈጥሯዊ ይዘት የማዛባት ህገወጥ ድርጊት መስተዋሉን አክለዋል።
እነዚህን ከምግብ ደህንነት አንፃር ፈፅሞ ተቀባይነት የሌላቸውን ድርጊቶች በህግ አግባብ ለመቆጣጠርና የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ኮሚሽኑ አዲስ የህግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ለማስጸደቅ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ አዲስ የሚወጣው ረቂቅ ደንብ ጸድቆ ወደ ስራ ሲገባ ከእርባታ እስከ ገበያ ያለውን የወተት ሰንሰለት ጥራት በማስጠበቅ ጤናማና ደህንነቱ የተረጋገጠ ምርት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
#አሐዱ_ሬዲዮ

20 hours ago