የሙዚቃው አበጋዝ ምሽት!
አንጋፋ የኪነጥበብ ምሽት!
የዛሬ ሁለት ሳምንት በ61ኛ ምሽት ወደክብር መድረኩ ይመለሳል!
በቤታችን፣ ኪነጥበብ እንደ ወንዝ ይፈሳል! በ60 ምሽቶች ያሳለፍናቸው ደማቅ ዝግጅቶቻችን አይረሴ ትዝታዎቻችሁ እንደሆኑ እምነታችን ነው፡፡
አሁን ለ61ኛ ጊዜ ሲፈስ፣ ጽዋው በከፍታ የሚነሳለት የክብር እንግዳችን በኢትዮጵያ ሙዚቃ የታሪክ ጉዞ ሂደት ውስጥ ወርቃማ አሻራውን በደማቁ ያተመው፤ አንጋፋው ጠቢብ፤ ታላቁ የሙዚቃ ቃና ባለሟል አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዮታ ነው!
የሙዚቃውአበጋዝ ምሽት!
በዚህ ታሪካዊ ምሽት ታላቁ የሙዚቃ ጥበብ ባለሟል በሦስት ትውልዶች ሕብራዊ ድምጽ ስሙ በክብር ይነሳል! ይመሰገናል!! በሥራዎቹ እየተወደሰ ይዘከራል!!!
ከሕይወት ጉዞው፤ ከሙዚቃ ፍልስፍናው፤ ከፈጠራ ሂደቱ፤ ከመድረክና ከስቱዲዮ ትዝታዎቹ፤ ከዘመን ዘመን የተሻገረ የጥበብ ልምዱን በልዩ አቀራረብ እየዋጀናቸው እናያቸዋለን፤ እንሰማቸዋለን።
የክብር መድረኩ የእርሱ ነው፤ ለክብሩ ዝነኞቹ ድምጻዊያን ይዘፍናሉ።(እነማን ናቸው?..... ምስጢር ነው)
የጥበብ ማዕዳችን ሰፊ፤ ገበታችንም ሙሉ ነው! ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃ፣ ሂስ፣ ዳንስና ፋሽን ሾው እንደተለመደው አይነት በአይነት ተዘጋጅተውላችኋል፡፡
📅 ረቡዕ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 ዓ.ም.
🕠 11:30 ሰዓት
📍 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል፣ ስድስት ኪሎ ግቢ
አንድ ምሽት፣ ብዙ ታሪኮች
አንድ መድረክ፣ ሺ ስሜቶች።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
(ሼር በማድረግ የጥበብ ግብዣውን ለሌሎችም አድርሱልን።)

1 day ago