Logo
FastMereja
13ኛ ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር
አዲስ ዓመትን በተስፋ እና በሕይወት እንቀበል

መስከረም 30 እና ጥቅምት 1, 2019 ዓ.ም.በኢትዮጵያ 20+ ከተሞች

አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል።
አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን ይዞ ይመጣል። በዚህ የበዓል ወቅት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ተስፋ እንሁን።

በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ሕክምና ላይ ላሉ ሕፃናት፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።

ይህ 13ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር በአዲሱ ዓመት የሕይወት ስጦታን ለመጀመር የሚያስችለን የሰብዓዊነት ጥሪ ነው።

እርስዎ የሚለግሱት ደም...
ለአንድ ልጅ ነገን፣
ለአንድ ቤተሰብ ተስፋን፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወትን፣
ለአንድ እናት ፈገግታን ሊሰጥ ይችላል።

በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና መላው ማኅበረሰብ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።

አዲስ አበባ ያላችሁ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የቀይ መስቀል ጊቢ የደም ልገሳው የሚደረግ ሲሆን በየክልሎቹ በሚገኙ የደም ባንክ ቅርጫፎች በመሄድ ደም እንድትለግሱ ጥሪ እናስተላልፋለን

ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!

ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ!

17 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.