Logo
TIKVAH-SPORT
ላሊጋ የካርቫልን ዝውውር አስቁሟል !

ሄታፌ ስፔናዊውን የቀኝ መስመር ተሰላፊ ዳኒ ካርቫል ለማስፈረም መስማማታቸው ተገልፆ ነበር።

ይሁን እንጂ የክለቡ ፕሬዝዳንት የተጨዋቹ ዝውውር መቋረጡን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

ሄታፌ ለማስመዝገብ ያቀረበው የዳኒ ካርቫል ደሞዝ በፋይናንስ ኮሚቴው አመኔታ እንዳላገኘ ተነግሯል።

ክለቡ ለዳኒ ካርቫል አመታዊ 400ሺህ ዩሮ ደሞዝ ለማስመዝገብ መጠየቁ ተገልጿል።

ዳኒ ካርቫል በሪያል ማድሪድ ቤት 10 ሚልዮን አመታዊ ክፍያ ያገኝ የነበረ በመሆኑ ላሊጋው ሀሰተኛ ነው በሚል ውድቅ አድርጓል።

@tikvahethsport      kidusyoftahe ዳኒ ካርቫል ወደ ሄታፌ ? ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ዳኒ ካርቫል ሄታፌን ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። የላሊጋው ክለብ ሄታፌ ዳኒ ካርቫልን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም እየሰራ መሆኑን አረጋግጧል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ከስምምነት ባይደረስም ንግግሮች የተሻለ ደረጃ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። ዳኒ ካርቫል በዚህ ክረምት ሪያል ማድሪድን ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ መልቀቁ አይዘነጋም።…
20 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.