ክፍያ እና ብድርን የሚያሳልጥ የዲጂታል ክፍያ ስርዓትን በ100 ሺህ ለሚቆጠሩ ነጋዴዎች ተደራሽ ለማድረግ ስምምነት ተደረገ
ስምምነቱን ያካሄዱት ኢታ ሶሉሽንስ እና ቪዛ ናቸዉ ። ለነጋዴዎች ክፍያን የሚያቀል ፣ ንግድን የሚያዘምን እና የዲጂታል ግብይት ታሪካቸዉን መነሻ በማድረግ ብድር የሚያመቻቸዉ "ዙሪያ "የተሰኘዉን ዲጂታል የቢዝነስ አዉቶሜሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ነጋዴዎች ለማዳረስ ስምምነቱን አካሄደዋል ።
የኢታ ሶሉሽንስ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ተመስገን ገብረህይወት እንደተናገሩት ስምምነቱ ዙሪያ የተሰኘዉን የዲጂታል ክፍያ መቀበያ ማሽን ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ 148 ሺህ ነጋዴዎች ለማድረስ የተደረገ ነዉ ማለታቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
ለነጋዴዎች በካርድ ፣ በኪዉአር (QR) ኮድ ፣የሞባይል ገንዘብ እና ከሂሳብ ወደ ሂሳብ የሚደረጉ ክፍያዎችን በአንድ መሳሪያ ላይ ማስተናገድ የሚቻልበት ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል ።
ይህንንም የካርድ ክፍያ ከትልልቅ ሱቆች ጀምሮ እስከ ጥቃቅን መደብሮች ተደራሽነቱን ለማስፋቱ እየተሰራ መሆኑ የተገለፀዉ ። ይህም ቴክኖሎጂ ለነጋዴዎች የዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በቀላሉ ለማወቅ ከማስቻሉም በዘለለ በግብይት ታሪካቸዉ ላይ በመመስረት የብድር ተጠቃሚ የሚሆኑበትንም ዕድል ያሰፋል ነዉ የተባለዉ ።
ኢታ ሶሉሽንስ ከአለምአቀፉ የብድር ተቋም ጋር በመተባበር ከባንኮች ጋር የብድር ስምምነት ይደርጋል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዉ በግብይት እንቅስቃሴያቸው ብቁ የሆኑ ነጋዴዎች የብድር ተጠቃሚ ይሆናሉ ማለታቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል

3 days ago