Logo
Getu Temesgen
የሉሲዎቹ ድንቅ ድል! ኢትዮጵያ ሩዋንዳን 1–0 አሸነፈች
#ethiopia | ለ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድር በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም የተጫወተው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን — ሉሲዎቹ — ከሜዳቸው ውጪ የሩዋንዳ አቻቸውን 1–0 በማሸነፍ ጠቃሚ ድል አስመዝግበዋል።

በጠንካራ ፉክክር የታጀበው ጨዋታ ብቸኛዋ ግብ በመጀመሪያው አጋማሽ ጭማሪ ደቂቃ፣ በ45+3ኛው ደቂቃ ላይ ተቆጥራለች። ግቧንም የሩዋንዳዋ ተጫዋች ኡዛዬሴንጋ ሊድያ በራሷ መረብ ላይ በማስቆጠር ሉሲዎቹን ወደ መሪነት አሸጋግራለች።

የዛሬው ከሜዳ ውጪ የተገኘው 1–0 ድል ሉሲዎቹን ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር ለማለፍ ጥሩ ዕድል የፈጠረላቸው ሲሆን፣ የመልስ ጨዋታው በጥቅምት 3 ቀን በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።

ሉሲዎቹ የጀመሩትን ድል በመልሱ ጨዋታ ያስጠብቁ!
#ኢትዮጵያ #ሉሲዎቹ #እግርኳስ #ኦሊምፒክማጣሪያ #ኢትዮጵያከሩዋንዳ #ethiopia #lucy #football

4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.