ሰበር መረጃ❗
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ይበልጥ ጠልቆ በመግባት ከመቀሌ ቀጥላ ክልሉ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችውን አዲግራትን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮነነ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ የዜና አውታር እንደተናገሩት፣ "በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም የጊዜ ገደብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለቀው መውጣት አለባቸው" በማለት የመንግስትን ጥብቅ አቋም አንጸባርቀዋል። ምንም እንኳን የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መኖሩ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ መኮንኖች ሲነገር ቢቆይም፣ የሚኒስትሯ የዛሬው መግለጫ ግን ኤርትራ ጦሯን በቀጥታ በማስገባት ሉዓላዊ አገር መውረሯን የሚያረጋግጥ "ይፋዊ የመንግስት ማረጋገጫ" ሆኖ ተመዝግቧል።
Seledadotio

2 days ago