በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንዲቀርበለት የሚያዘው ደንብ በስራ ላይ ውሏል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግሥት የሚሰጠውን የብሎክ ግራንት የበጀት አፈጻጸም ለመደንገግ ያወጣው ደንብ ቁጥር 594/2018 በስራ ላይ ውሏል።
ደንቡ ተቋማቱ በፋይናንስ ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ በሂደት እየቀነሰ የሚሄድ ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ የሚመደብበትን ሥርዓት ያካተተ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎቻቸውና ስትራቴጂካዊ ዕቅዶቻቸው በመነሳት በበጀታቸው በነፃነት እንዲጠቀሙና ተልዕኳቸውን በጥራት እንዲወጡ ማስቻልን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ያስረዳል።
ደንቡ ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው ዓመታዊ የብሎክ ግራንት እንደ አግባብነቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲባል፣ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ነገር ግን የትምህርት ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ተማሪዎች የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሊያካትት እንደሚችል ያስረዳል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች በሚያስተዳድሯቸው ማስተማሪያ ሆስፒታሎች አማካኝነት፣ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶች እና በነፃ ማግኘት ለሚገባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የበጀት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻልም ሊመደብ እንዲሚችል ይገልጻል።
እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያከናውኗቸውን የምርምርና ጥናት፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት አገልግሎት እንዲሁም ብቁ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልግ የፋይናንስ ድጋፍ ሊመደብ እንደሚችል ተደንግጓል።
በዚህ ደንብ መሠረት አጠቃላይ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት ድልድል የግብዓት፣ የውጤትና የፍትሐዊነት መስፍርቶችን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ይህም
• የመማር-ማስተማር ሂደቱን መደበኛ ተማሪዎች ቁጥር፣
• የሳይንሳዊ ምርምር ውጤትና ተፅዕኖን፣
• የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎችን እንዲሁም
• ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን እና የተቋማቱን መልክዓ-ምድራዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ታሳቢ ያደርጋል።
ይህ የበጀት ማከፋፈያ ቀመር እንደ አስፈላጊነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማጣጣም በየሁለት ዓመቱ ክለሳ ይደረግበታል።
በተለየ መልኩ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግለት ተደንግጓል።
ይህ ድጋፍ ሆስፒታሎቹ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶችና ተጠቃሚ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ሲሆን፤ ድልድሉም በሆስፒታሉ አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች ብዛት፣ የህክምና አልጋዎች ቁጥር፣ የአገልግሎቶቹ ውስብስብነት እንዲሁም ለመድኃኒትና ለአላቂ የሕክምና ቁሳቁሶች የሚወጣውን ወጪ መሠረት በማድረግ ይወሰናል።
በዚህም ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሚያገኘው ዓመታዊ ድጋፍ አጠቃላይ የመማር-ማስተማርና የምርምር በጀቱን እንዲሁም ለማስተማሪያ ሆስፒታሎች በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚመደበውን ልዩ በጀት በአንድ ላይ ያካተተ የተቀናጀ የብሎክ ግራንት ሆኖ ይቀርባል።
የበጀት ጥያቄ አቀራረብና አስተዳደርን በተመለከተ፣ ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የበጀት ጥያቄውን በየዓመቱ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለገንዘብ ሚኒስቴር ማቅረብ እንዳለበት እና የተፈቀደው በጀትም በቀጥታ ወደ ተቋማቱ ፈሰስ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከርም ትምህርት ሚኒስቴር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች ላይ የተመሠረተ የአፈጻጸም ውል በመፈራረም በዓመት ሁለት ጊዜ ሁለንተናዊ ግምገማ እንደሚያካሂድ ተደንግጓል።
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዎቹ የብሎክ ግራንት ሒሳብ በፌደራል ዋና ኦዲተር እንደሚመረመርና የሒሳብ ሰነዶችም ቢያንስ ለአስር ዓመታት ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረግ ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሰፍን ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

2 days ago