ኤርትራ "ኢትዮጵያ ራስን በመከላከል ስም ልትወረኝ ነው" ስትል ከሰሰች
#fastmereja I የኤርትራ መንግሥት ፕሬስ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት "ሉዓላዊ የባህር በር ማግኘት" እና የባህርኃይል አቅምን ለመገንባት በሚል ሽፋን በኤርትራ ላይ የጥቃት ጦርነት ለመክፈት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው አለ። የኤርትራ መንግሥት ቃለ አቀባይ የማነ ገብረመስቀል ከሰዓታት በፊት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በኤርትራ ላይ የሐሰት ውንጀላዎችን በመሰንዘር አጀንዳቸውን በ"ራስን የመከላከል" ስም ለመሸፈን እየሞከሩ ነው ብለዋል።
በመግለጫው እንደሰፈረው፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የተሰሙ ከፍተኛ የሰራዊት ጄኔራሎች አስተያየቶች የኢትዮጵያን እውነተኛ አላማ የሚያሳዩ ናቸው። በተለይም አንድ ከፍተኛ ጄኔራል ለአገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃል "ዘመቻውን ስንጀምር ትግራይ ላይ አንቆምም... ዋናው አላማችን ባንዲራችንን ቀይ ባህር ላይ ማቆም ነው" ማለታቸው አሳሳቢ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት አመልክቷል። እንዲሁም "መቀሌ ማቆሚያ አይደለችም፣ የመጨረሻ መድረሻችን አሰብ ነው" የሚሉ ንግግሮች የኢትዮጵያን እቅድ ግልጽ የሚያደርጉ እንደሆኑ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሆን ብሎ ጦርነቱን በራስን መከላከል ስም ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ቀባይነት የሌለው እና ክልላዊ ጸጥታን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል የኤርትራው ቃለ አቀባይ ማነ ገብረመስቀል በመግለጫቸው ገልጿል።

4 days ago