Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ከተማ የ2019 ዓ/ም የሁሉም እርከን የተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 30 ቀን እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳሰበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ከቅድመ-አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲያካሂድ የቆየው የተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።

ቢሮው ለነባር ሆነ ለአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በቂ ጊዜ መስጠቱን በመጥቀስ፣ ከጥቅምት 01 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም እርከን ምንም ዓይነት የተማሪዎች ምዝገባ እንደማይካሄድ ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች በጻፈው ሰርኩላር አሳስቧል።  

ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://www.facebook.com/s...

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.