የትግራይ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ እንዲሰባሰቡ መንግስት ጥሪ አቀረበ
የብሔራዊ ተሃድሶ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው የትግራይ ሠራዊት አባላት ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ አካባቢ በተዘጋጀው የተሃድሶ ማዕከል እንዲሰባሰቡና ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ።
ምክትል ኮሚሽነሩ በቪዲዮ በተሰራጨው አጭር መልዕክታቸው፤ የመንግሥት ጥሪን በመጠበቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ታጣቂዎች እንዳሉ ገልጸው፣ ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ ወደተዘጋጀው የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል መግባት እንደሚቻል አስታውቀዋል።
ጄኔራሉ፤ ለመልሶ ማቋቋምና ተሃድሶ (ዲ.ዲ.አር) ፕሮግራም የተዘጋጁ በርካታ ወጣቶች መኖራቸውን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ሰላም ለመምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በርካታ ታጣቂዎች በየአካባቢው በሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒቶች እጅ እየገቡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ መንግሥት ለብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስፈላጊውን በጀት መመደቡንና ኮሚሽኑም ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በተጨማሪም የትግራይ ወጣቶች ከጦርነት እሳት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱና የልማት ኃይል እንዲሆኑ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኩል ከፍተኛ ድጋፍ መኖሩን አስረድተዋል።
በመሆኑም ታጣቂዎች በየአካባቢው ለሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒቶች በግለሰብም ሆነ በተደራጀ መንገድ ሪፖርት በማድረግ፣ የጦር መሣሪያና ወታደራዊ ቁሳቁሶቻቸውን በማስረከብ በመቀሌ አካባቢ ወደተዘጋጀው የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል እንዲገቡ ጥሪ ቀርቧል።
ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ በመግለጫቸው “ወጣቱ ለተወሰኑ ጽንፈኞችና ግለሰቦች ዓላማ ተብሎ በጭፍን ማለቅ የለበትም፤ ሁሉም ጨለማ አይደለም፣ ብርሃን አለ” ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም መጀመሪያ ላይ በራሳቸው ፍላጎት የተቀላቀሉም ሆነ በኋላ ላይ ተገድደውና ታፍሰው የገቡ ወጣቶች አማራጭ እንዳለ አውቀው ወደ መንግሥት እንዲገቡ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ታጣቂዎቹ ወደ ተሃድሶ ማዕከላት በመግባት ተሃድሶ ከወሰዱ በኋላ፣ በመልሶ ማቋቋምና በመልሶ ማደራጀት ሥራ ውስጥ ተካተው የራሳቸውን፣ የቤተሰቦቻቸውን፣ የትግራይ ክልልን እንዲሁም የሀገርን አቅም መገንባት እንዲችሉ ኮሚሽኑ ጥሪውን ያቀረበ ሲሆን፣ ከዛሬ ጀምሮ በመቀሌ በተዘጋጀው የተሃድሶ ማዕከል መግባት እንደሚቻል ተገልጻል።
Seledadotio

2 days ago