(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጆርጌ ጂሰስ ጋር ስለተፈጠረው አለመግባባት እና በቡድኑ ውስጥ ስላለው ቀጣይ ቆይታ ዝርዝር ማብራሪያ የሚሰጥ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል። ሮናልዶ በራሱ አንደበት ባወጣው በዚህ መግለጫ፣ አሰልጣኙ የገቡለትን ቃል በማጠፍ ክህደት እንደፈጸሙበት በግልጽ አስታውቋል።
ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በኋላ ከብሔራዊ ቡድኑ በይፋ ለመሰናበት የመሰናበቻ ደብዳቤ አዘጋጅቶ እንደነበር ያስታወሰው ሮናልዶ፣ የፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ውሳኔውን ዳግም እንዲያጤነው እና በቡድኑ እንዲቀጥል አጥብቀው እንደጠየቁት ገልጿል። በወቅቱም ፕሬዝዳንቱ አዲሱን አሰልጣኝ ጆርጌ ጂሰስን ሹመት በተመለከተ የሮናልዶን አስተያየት የጠየቁ ሲሆን፣ ሮናልዶም ለእርሳቸው መሾም ሙሉ ድጋፉን ሰጥቶ እንደነበር አብራርቷል።
ጂሰስ ከተሾሙ በኋላ ሁለቱ አካላት ሮናልዶ በሚጫወትበት የአል ናስር ክለብ የቅድመ ውድድር ልምምድ ማዕከል በአካል ተገናኝተው ተወያይተዋል። በውይይቱም አሰልጣኙ ሮናልዶ ለመጪው ፕሮጀክታቸው ወሳኝ መሆኑን ነግረውት፣ የአካል ብቃቱን ለመጠበቅ በሚል የመጀመሪያውን እና የመጨረሻውን ጨዋታ ብቻ እንዲጫወት፣ ወደ ኖርዌይ እና ዴንማርክ ከቡድኑ ጋር እንዳይጓዝ ሃሳብ አቅርበውለት ነበር። ነገር ግን ሮናልዶ "የቡድኑ አምበል ሆኜ አብሬ አለመጓዝ መጥፎ አርአያነት ነው" በማለት ሃሳቡን ወዲያውኑ ውድቅ ማድረጉን እና አሰልጣኙም በውሳኔው መስማማታቸውን አስታውቋል። ይህ ውይይት በተካሄደበት ወቅት አሰልጣኝ ጂሰስን በ2025 ወደ ክለቡ በማምጣት ትልቅ ሚና የነበራቸው የአል ናስሩ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሲማኦ ኩቲንሆ በስፍራው እንደነበሩ ሮናልዶ አክሏል።
ከስምምነቱ በኋላ ሮናልዶ በአልቫላዴ ስታዲየም በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን፣ ተቀይሮ ሲወጣም የአምበልነቱን ማዕረግ ለብሩኖ ፈርናንዴዝ አስረክቦ ነበር። ሮናልዶ ይህ ድርጊቱ ምናልባትም በብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻው ተሳትፎ ሊሆን እንደሚችል በወቅቱ እንዳላሰበ ተናግሯል።
ዋነኛው ችግር የተፈጠረው ግን በኖርዌዩ ጨዋታ ላይ ነው። በእለቱ ሮናልዶ በድራጋዎ ስታዲየም ለሚደረገው ቀጣይ ጨዋታ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ እረፍት እንዲያደርግ በቅድሚያ ስምምነት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፣ የምሳ ሰዓት ላይ የአሰልጣኙ ረዳት መጥቶ ጂሰስ እንደሚፈልጉት ነገረው። ጂሰስም በድንገት "ለ30 ደቂቃ መጫወት ትችላለህ ወይ?" ሲሉ እንደጠየቁትና እሱም ከቅድመ ስምምነታቸው ውጪ ቢሆንም ጥያቄውን ተቀብሎ ፈቃደኛ መሆኑን እንደገለጸላቸው ሮናልዶ አብራርቷል።
ነገር ግን ሮናልዶ ከእረፍት ሰዓት ጀምሮ የሟሟቂያ ልምምድ እያደረገ ሙሉ 45 ደቂቃዎችን ቢያሳልፍም፣ አሰልጣኙ ወደ ሜዳ ሳያስገቡት ጨዋታው ተጠናቋል። ሮናልዶ መግለጫውን ሲያጠቃልል፣ "ከዚያ በኋላ የሆነውን ሁሉም ሰው ያውቃል። አሰልጣኙ ለእኔ የገቡትን ቃል አጥፍተዋል" በማለት የጆርጌ ጂሰስን ተግባር በጽኑ ኮንኗል።

2 days ago