በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ጌጣጌጦችን የሰረቀች ግለሰብ ከነ አባሪዎቿ በቁጥጥር ስር ዋለች።
ኢየሩሳሌም በርገኔና አማኑኤል ማቲዮስ የተባሉ ተጠርጣሪዎች አባሪና ተባባሪ በመሆን የስርቆት ወንጀሉን የፈፀሙት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዲቦራ ፋውንዴሽን ተብሎ ከሚጠራባት ከጠዋቱ 3 ሠዓት አካባቢ ነው ።
ተጠርጣሪዋ ለ 1 ዓመት ከ5 ወር ያህል የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስትሰራ የነበረች ሲሆን በቤት ውስጥ የነበሩት የእጅ የወርቅ ሰዓት የዋጋ ግምቱ 4 ሚሊዮን 74ሺ 250 ብር፣ 2 የዳይመንድ የእጅ ሰዓት የዋጋ ግምታቸው 2ሚሊየን 149ሺ 600 ብር፣ 1 የጆሮ ጌጥ የወርቅ ያልተመለሰ ግምቱ 126 ሺህ እንዲሁም የተለያዩ ጌጣጌጦች የዋጋ ግምታቸው 5ሺህ ብር፣ 2 የወርቅ ቅብ የእጅ ሰዓት ግምታቸው 3 መቶ 88 ሺህ እና ሌሎች የተለያዩ የዋጋ ግምት ያላቸውን ጌጣጌጦችን ምቹ ሁኔታን በመጠቀም ሰርቃ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ለሚኖር የወንድ ጓደኛዋ ጋር በአደራ ታስቀምጣለች።
የግል ተበዳይም መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም ወደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ላንቻ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
የግል ተበዳይን ጥቆማ መሠረት በማድረግ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡ የተጠርጣሪዋ ፍቅረኛ የሆነው አማኑኤል ማትዮስ ከ 4ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣውን 1 የእጅ የወርቅ ሰዓት በ540ሺ ብር አብዱልአፊዝ ነጂብንም ለተባለ ግለሰብ የሸጠ ሲሆን ፖሊስ ገዢውንም በቁጥጥር ስር አውሏል።
ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቶቹን ለባለቤቱ ያስመለሰው ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በመሰብሰብ ምርመራው በተገቢው መልኩ ቀጥሏል፡፡
ፖሊስ በክፍሉ ዓቃቤ ህግ በኩል ክስ ለመመሰረት ዝግጅት ላይ ሲሆን ያልተመለሱ ንብረቶችን ለማስመለስም ምርመራ የማስፋት ተግባራት መቀጠላቸውን የላንቻ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጌታደጉ ወርቁ ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛን ሲቀጥር በቂ ተያዥ መኖሩን ማረጋገጥ እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ውድ ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ላይ በቂ ጥንቃቄና ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበትም መልዕክቱን አስተላልፏል።

4 days ago