(ዘ-ሐበሻ መዝናኛ ዜና) ታዋቂው አሜሪካዊ አርቲስት ክሪስ ብራውን አሁን ካለችው ፍቅረኛው ጃዳ ዋላስ ጋር አዲስ ልጅ ከማግኘቱ ጥቂት ቀናት አስቀድሞ፣ በልጅ ሞግዚትነት ጥያቄ የፍርድ ቤት ክስ እንደቀረበበት ተዘገበ።
እንደ ቲኤምዚ የዜና ዘገባ፣ የክሪስ ብራውን የቀድሞ ፍቅረኛ ዳይመንድ ብራውን የተወለደችውን የ4 ዓመቷን ልጃቸውን በተመለከተ በሚያዝያ 3 ሙሉ የህጋዊ እና አካላዊ ሞግዚትነት መብት እንድታገኝ ክስ መስርታለች። በክሱ ላይ ክሪስ ብራውን ልጁን የመጠየቅ መብት ሊሰጠው እንደሚችል የገለፀች ሲሆን የፍርድ ቤቱን ወጪ ግን ሙሉ በሙሉ እሱ እንዲሸፍን ጠይቃለች።
ይህ የህግ ሂደት ከመጀመሩ ጥቂት ሳምንታት በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በዳይመንድ እና በአዲሷ የክሪስ ፍቅረኛ ጃዳ መካከል የቃላት ምልልስ ተፈጥሮ ነበር። ጃዳ፣ ዳይመንድ ክሪስን ልጁን እንዳያይ እየከለከለች ነው በማለት ስትወቅስ፤ ዳይመንድ ግን ይህንን አስተባብላ ክሪስ በአንድ ወቅት ባሳየው ፀባይ ምክንያት ከአንዴ ውጪ ልጁን እንዳያይ ከልክላ እንደማታውቅ ተናግራለች።

3 days ago