በመስከረም ወር ከ2ሺ በላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን የፍልስጤም ኮሚሽን አስታወቀ
የፍልስጤሙ የዜና ወኪል ዋፋ የቅጥር እና ሰፈራ መከላከያ ኮሚሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በመስከረም 2026 የእስራኤል ኃይሎች እና ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን፣ መሬት እና ንብረታቸው ላይ 2ሺ 51 ጥቃቶችን ፈጽመዋል።
ከዚህ አጠቃላይ ቁጥር ውስጥ 1ሺ 404ቱ በእስራኤል ኃይሎች የተፈጸሙ ሲሆን፣ 647ቱ ደግሞ በሰፋሪዎች የተፈጸሙ ናቸው። በሌላ በኩል ራማላህ እና አል-ቢራህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥቃቶች የተመዘገቡባቸው ከተሞች መሆናቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።
በሰፋሪዎች በተሰነዘረ ጥቃት የሶስት ፍልስጤማውያን ህይወት ማለፉን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ይህም የ2026ቱን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 29 ከፍ ማድረጉን እና በሌሎች 88 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ማድረሱን አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ጥቃቶቹ 9ሺ 334 የወይራ ዛፎችን ጨምሮ በ14ሺ 600 ዛፎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
የእስራኤል ባለስልጣናት የመሬት ንጥቂያ እና የዛፍ ምንጠራ ትዕዛዞችን ማውጣታቸውን በቀጠሉበት በዚህ ወቅት፣ አዳዲስ ህገ-ወጥ የሰፈራ ጣቢያዎችን ለመመስረት 21 ሙከራዎች መደረጋቸው ተዘግቧል።
የእስራኤል ባለስልጣናት 254 ግንባታዎችን ያወደሙ 62 የማፍረስ ዘመቻዎችን ማካሄዳቸውን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ይህ ድርጊት 164 ህጻናትን ጨምሮ 320 ፍልስጤማውያንን በቀጥታ የጉዳቱ ሰለባ ማድረጉን አብራርቷል።
#ዳጉ_ጆርናል

8 days ago