Logo
AHADU RADIO FM 94.3
"የኢሬቻ በዓል የመልካም ምኞት፣ የምስጋና እና የሰላም መግለጫ ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ የኢሬቻ በዓል ክረምቱ በሰላም አልፎ ለብርሃንና ለበጎ ነገር በመበቃቱ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት፣ የምስጋና እና የሰላም በዓል መሆኑን ገልጿል።

የበዓሉ መከበር የኦሮሞ ህዝብን ባህል፣ ቋንቋ እና አባታዊ እሴቶች የሚያጎላና ወደ መደበኛው ስርዓት ተመልሶ በድምቀት እንዲከበር የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት፤ ሀገሪቱ ያጋጠሟታትን አስቸጋሪ ወቅቶችና የክረምት ጨለማዎች በመሻገር ወደ መልካም ምዕራፍ ተሸጋግራለች ብለዋል።
በተለይም የሕዳሴው ታላቅ ግድብ ውኃ ሙሌት መጠናቀቅ፣ ሀገራዊ የምክክር ሂደቶች፣ የከተሞች የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች እና የቦሌ አቪዬሽን ከተማ ፕሮጀክት አዲሱ የስልጣኔና የብልጽግና ምዕራፍ ማሳያዎች መሆናቸው ተገልጻል።
መግለጫው አክሎም፤ የመደመር ፍልስፍናን መሰረት በማድረግ የጋራ እውቀትን፣ ፍትሃዊ ስርዓትንና ደህንነትን በመገንባት ሀገራዊ ስልጣኔን እውን ለማድረግ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብሏል።

በተጨማሪም፤ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን የሀሳብ ልዩነቶችን በመደማመጥ ለመፍታት የሚያስችሉ የሰላም ስርዓት ስራዎች መከናወናቸው ተመላክቷል።

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.