አንድ የግመል የእንባ ጠብታ እስከ 26 የሚደርሱ የእባብ መርዞችን ሊያስወግድ እንደሚችል ሳይንሳዊ ግኝት ይፋ ሆነ
#ethiopia | በቅርብ ጊዜ በተደረገ ጥናት መሰረት፣ አንድ የግመል የእንባ ጠብታ እስከ 26 የሚደርሱ የእባብ ዝርያዎችን መርዝ የማስወገድ አስደናቂ አቅም እንዳለው ሳይንቲስቶች ገለጹ።
ይህ ግኝት በተለይም የእባብ ንክሻ በብዛት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ለሕይወት አድን መድኃኒቶች ልማት አዲስ ተስፋ የሰነቀ ነው ተብሏል።
በዱባይ የሚገኘው ማዕከላዊ የእንስሳት ህክምና ምርምር ላብራቶሪ ባደረገው ጥናት፣ የግመል እንባ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ባዮአክቲቭ ውህዶች (bioactive compounds) እና ፀረ እንግዳ አካላት (antibodies) የተለያዩ የእባብ መርዞችን የመከላከል አቅም እንዳላቸው ተመላክቷል።
እነዚህ ውህዶች በነርቭ ሥርዓት ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ኒውሮቶክሲን እና የደም ሴሎችን የሚያበላሹ ሄሞቶክሲን የተባሉ መርዞችን ጭምር ማምከን እንደሚችሉ ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።
ይህ ግኝት ገና በሳይንሳዊ መጽሔቶች ላይ ባይታተምም፣ የእባብ ንክሻ ሕክምናን አብዮታዊ በሆነ መንገድ ሊለውጥ ይችላል ተብሎለታል።
በተለይም በገጠር አካባቢዎች ለሚኖሩ እና ለባህላዊ የእባብ መርዝ ማስታገሻ (antivenom) የመድኃኒት አቅርቦት ለሌላቸው ማህበረሰቦች ተመጣጣኝ እና ውጤታማ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ተደርጓል።
ከመርዝ ማስወገድ አቅሙ በተጨማሪ፣ የግመል እንባ በደረቅ አካባቢዎች እንስሳውን ከኢንፌክሽኖች ለመጠበቅ የሚያስችሉ ፕሮቲኖች እና ላይሶዛይም (lysozyme) የተባለ ጠንካራ ፀረ-ባክቴሪያ ኢንዛይም የያዘ መሆኑም ተመራማሪዎቹ አክለው ገልጸዋል።
ይህ ጥናት የግመሎችን ሚና ከጭነት እንስሳነት ባሻገር ለህክምና መስክ ያላቸውን አስተዋፅዖ በድጋሚ ጎላ አድርጎ አሳይቷል ተብሏል።
ይህ ግኝት ወደፊት ተጨማሪ ጥናቶች ከተደረጉበት እና በሳይንሳዊ መንገድ ከተረጋገጠ፣ በየዓመቱ በእባብ ንክሻ ለሚሞቱ ወይም የአካል ጉዳት ለሚደርስባቸው በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች አዲስ ተስፋ ሊሰጥ ይችላል ነው የተባለው። #menahriafm

11 months ago