Logo
SeledaPost
በደቡባዊ ትግራይ አላማጣ እና ማይጨው እንዲሁም በቆቦ ከተሞች አካባቢ በሚካሄደው ግጭት ከ70 በላይ ንጹኃን ሳይገደሉ እንዳልቀረ የሚጠቁሙ መረጃዎች እንደደረሱት ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ ገለጠ።

በተጠቀሱት አካባቢዎች የንጹኃን ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በተለይ በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን የሽራሮ፣ ሽሬ እና አክሱም ከተሞች ነዋሪዎች የምግብ፣ የውሃና የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸው የገለጠው ድርጅቱ፣ የታጠቁ ኃይሎች ንጹሐንና የጦርነት ተሳታፊዎችን ለይቶ የማየት ግዴታ እንዳለባቸው አሳስቧል።

ፌደራል መንግሥቱና ታጣቂ ኃይሎች ንፁኃን ሰዎችን ከጥቃት እንዲጠብቁ፣ አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን እንዲያቆሙ፣ የመብት ጥሠቶችን እንዲመረምሩና በንፁኃንና በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችም ባስቸኳይ እንዲቆሙ ድርጅቱ ጠይቋል።

Seledadotio
Seledadotio
8 days ago
Administrator
8 days ago
Replying to SeledaPost 's post

Administrator sent a gift to SeledaPost

10$

Gift note
testing
Administrator
8 days ago
Replying to SeledaPost 's post
test
Administrator
8 days ago
Replying to SeledaPost 's post

Administrator sent a gift to SeledaPost

10$