Logo
AHADU RADIO FM 94.3
ሐሰተኛ ሰነዶችን ለማረጋገጥ የሚያስችል ኢጌት (e-Gate) የተሰኛ አሰራር ተግበራዊ መደረጉ ተገለጸ፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ 2019 በጀት ዓመት የሰዎችን ማንነት እና ሀሰተኛ ሰነዶችን በቀላሉ በመለየት የሚያስችል ኢጌት (e-Gate) የተሰኛ አሰራር ተግበራዊ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይሄ አሰራር በተቋሙ ያለውን የተገልጋዮች ሰልፍ የሚያስቀር መሆኑን የገለጹት የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶአምቦ መቃሳ ናቸው።
ይህ ቴክኖሎጂ ፓስፖርት ወይም የመታወቂያ ካርድን በማንበብ እና የሰዎችን የፊት ገጽታ ወይም የጣት አሻራ በማመሳከር ያለ ሰው ንክኪ ፈጣን አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂው የሰዎችን ሰነድ በጥቂት ዳይቃዎች በመፈተሽ አገልግሎት ላይ ያለውን መጨናነቅ የሚያስቀር መሆኑን አንስተው ይሄ አሰራር በሌሎች ሀገራት ተግበራዊ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኢሚግሬሽን እና የደህንነት መረጃዎችን ከማዕከላዊ ዳታቤዝ ጋር በቀጥታ በማገናኘት የሐሰት ሰነዶችን በቀላሉ ለመለየት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢጌት (e-Gate) አገልግሎት መጀመሩ የሰው ኃይል ጉልበትን በመቆጠብ የደህንነት ሰራተኞች ይበልጥ ትኩረት በሚሹ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

በህይወቴ ጌትነት

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.