የባለሙያዎችን ፍልሰት ለመግታት የማበረታቻ ስርዓት ሊዘረጋ መሆኑን የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ገለጸ
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከፍተኛ ክህሎት ያላቸው የሕግ እና የታክስ ባለሙያዎች ተቋሙን ለቀው እንዳይሄዱ ለማድረግ አፈጻጸምን መሠረት ያደረገ የማበረታቻ ስርዓትና የሙያ ዕድገት መዋቅር ሊዘረጋ መሆኑን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ለአሐዱ ሬድዮ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፣ በ2019 የበጀት ዓመት ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ዋና ዋና ስጋቶች መካከል የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍልሰት እና የማስፈጸም አቅም ዝቅተኛነት በግንባር ቀደምትነት የተቀመጡ ናቸው።
ይህንን የሰው ኃይል ፍልሰት ለመከላከል ግልጽ የሆነ የሙያ ዕድገት መዋቅር ከመዘርጋት ባሻገር የሥራ አካባቢን ምቹ ማድረግ እና አፈጻጸምን መሠረት ያደረጉ ማበረታቻዎችን መተግበር እንደ መፍትሔ በሪፖርቱ ተካተዋል።
በተጨማሪም፤ በአገልግሎት ዘርፉ በሰው ኃይል የማስፈፀም አቅም ዝቅተኛነት እና የተገልጋይ እርካታ መቀነስ በበጀት ዓመቱ ተግዳሮት እንደሚሆኑ ኮሚሽኑ ጠቁሟል።
የተነሱትን ተግዳሮቶች መሠረት ያደረጉ መፍትሔዎችን ለመተግበር የቴክኖሎጂ ዘርፉ እንደሚጠናከር ተገልጿል።
በዚህም የመረጃ ስርዓቶችን በማላመድ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ ታቅዷል።
በዓለምነው ሹሙ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

11 days ago