በአርባ ምንጭ ከተማ ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ተገኙ፡፡
በአርባ ምንጭ ከተማ በሕገ-ወጥ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው የተገኙ እና በገበያ ፈቃድ ማረጋገጫ የሌላቸው አደገኛ ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣኑ ያስታወቀ ሲሆን ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከከተማው ፖሊስና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ባካሄደው ድንገተኛ የክትትል ሥራ በከተማው ሕገ-ወጥና ያልተፈቀዱ መድኃኒቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተናግሯል።
በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 38 መሠረት የመድኃኒቶችን ደህንነት የመከታተል ኃላፊነት የተሰጠው ባለሥልጣኑ፤ የተያዙት ምርቶች በሕገ-ወጥ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው የተገኙና የገበያ ፈቃድ የሌላቸው መሆናቸውን አረጋግጧል።የተረጋገጠ ጥራትና ደህንነት የሌላቸው ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች በታካሚዎች ላይ ከባድ የጤና አደጋ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የተሳሳቱ ወይም ጎጂ ንጥረ ነገሮች ሊኖራቸው እንደሚችልና ሕመምንም ሊያባብሱ እንደሚችሉ ተመላክቷል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ እነዚህን ምርቶች እንዳይጠቀም ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ ማንኛውም የጎንዮሽ ጉዳት ያጋጠመው አካል ከጤና ባለሙያ ዘንድ ቀርቦ ሕክምና እንዲያገኝ አሳስቧል።የጤና ባለሙያዎችና ሕብረተሰቡ እንዲህ ዓይነት ሕገ-ወጥ ወይም የተጭበረበሩ ምርቶች ሲያጋጥመው ከክፍያ ነፃ በሆነው በስልክ መስመር በ8482 ላይ በመደወል አሊያም በባለሥልጣኑ ድረ-ገጽ ላይ በሚገኘው ውብሳይት እና የ E-reporting አገልግሎት፣በመጠቀም ሪፖርት እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ አሳስቧል
#ዳጉ_ጆርናል

11 days ago