ሁለት ተሽከርካሪዎችን ከማቆሚያቸው ቦታ የሠረቁ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ተጠርጣሪዎቹ ኢብራሂም የኑስ፣ ነጅመድን ሬድዋን እና ኑረዲን በርጌቾ ሲባሉ ወንጀሉን የፈፀሙት መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም ከለሊቱ 9፡00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ሰሚት ኮንዶምኒየም 2ኛ በር አካባቢ ነው።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የጎሮ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ባሳዝነው አክሎግ እንደተናገሩት የግል ተበዳዮች እና የተሽከርካሪ ማቆሚያው ጥበቃ ኃላፊ በሰዓቱ በመምሪያው በአካል ቀርበው ተሽከርካሪ እንደተሰረቀባቸው አመልክተዋል፡፡
የፖሊስ መምሪያው የምርመራና የክትትል ቡድኑ ወንጀሉ ተፈጽሞበታል የተባለበት ቦታ በመሄድ ወንጀሉ መፈፀሙንም አረጋግጠዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3_59732 ኢት ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከቆመበት አንስተው በአካባቢው በመሸሸግ ሌላኛውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3_53262 ኢት የሆነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪን ደግመው ይዘው መሰወራቸውን በማረጋገጥ በጥብቅ ክትትል የስርቆት ወንጀል ድርጊቱ በተፈፀመ በ24 ሠዓት ውስጥ በሸገር ከተማ አስተዳደር አንፎ አደባባይ አካባቢ ተሽከርካሪውን አቁመው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ኮማንደር ባሳዝነው አክሎግ አክለውም ተጠርጣሪዎቹ ሲያዙ ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀሙበት የነበረ ባለቤትነቱ ለጊዜው ያልታወቀ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2_C15420 አ/አ የሆነ ራቫ ተሽከርካሪ የተያዘ ሲሆን በተደረገ ፍተሻም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 _A10747 ኢት የፊትና የኋላ እንዲሁም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3_65681 ኢት መገኘቱን ገልፀው፤ ተጠርጣሪዎቹ ሲያዙም ለወንጀል ድርጊት የሚጠቀሙባቸው የተሽከርካሪ ቁልፎች መገኘታቸውን ተናግረዋል።
የግል ተበዳይ የሆኑት አቶ ሀዱሽ ኃ/ስላሴ እና አቶ ፀሃዬ መሰለ የፖሊስ ስራ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን በመግለፅ በቴክኖሎጂ በተደገፈ መልኩ እየሰራ ያለው ስራ ተቋሙ የህብረተሰቡን ርካታ ለመፍጠር እየሄደበት ያለው ርቀት ማሳያ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡
የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ላይ ተደራጅተው የሚሰሩ አካላት በህጋዊ መንገድ ተያዥ ያለው ጥበቃ ከመቅጠር ባለፈ ቁጥጥርና ክትትል ሊያደርጉ ይገባል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ባለንብረቶችም ተሽከርካሪዎቻቸው ላይ ጂፒኤስ በማስገጠም ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

8 days ago